News News

የትምህርት ቤት ጤናና ምግብ ፕሮግራም ትግበራ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ

ይህ የተገለጸው የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከዓለም አቀፍ ለህፃን  ዕድገት አጋር ድርጅት (The Partnership for Child Development, PCD) ጋር በመተባባር ባዘጋጀው መድረክ ነው፡፡

 

ሚኒስቴር /ቤቱ ፕሮግራሙን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ  መጋቢት 04/07/2009 .ጤናማ መሆን ለመማር ለመማር ጤናማ መሆን የትምህርት ቤት ጤናና ምግብ ማሳደግበሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የልማት አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር የአንድ ቀን ምክክር አውደ ጥናት አካሂዷል፡፡

 

ፕሮግራሙ በመጀመሪያ ደረጃ የሚማሩ ህፃናት በምግብ እጥረትና በተለያዩ በሽታዎች ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቀሩና እንዳያቋሪጡ  ብሎም ትምህርታቸውንም በትኩረት እንዲከታተኩ የጎላ ሚና አለው፡፡

 

በየሚኒስቴር /ቤቱ  የትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ያሳቡ ብርቅነህ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታን በመወከል የመድረኩ መክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት እንደተናገሩት ተማሪዎች በአካላልና በአዕምሮ ዕድገት የተሸለ ሆኖ እንዲወጡ  የትምህርት ቤት ጤናና ስነ ምግብ ፕሮግራም ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 

በመረጃ የተደገፈ የትምርት ቤት ጤናና ምግብ ድጋፍ ማጠናከር፥   በመላው ሀገሪቱ የትምህርት ዘርፍ ልማት እቅዶችና ፖሊሲ  ለማሳካት የተረጋጋ፣ ወጪ ቆጣቢ እንዲሁም  ለረጅም ጊዜ የሚያገለግል  መርሃ ግብር መቅረፅ ነው ብለዋል አቶ ያሳቡ፡፡

 

እንደ ዳይሬክተሩ ንግግር  የተማሪዎች ትምህርት ውጤትና የመማር ፍላጎት ይበልጥ ለማሳደግ  ሚኒስቴር /ቤቱ ከፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከግብርናና የተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር እንዲሁም ከውኃና ኤልክትሪክ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተማሪዎች የመማር ሂደት የሚያሳኩ ጤናና  የምግብ ድጋፍ ለማድረግ በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ጨምሮ ጠቁመዋል፡፡  

 

በሚስቴር /በቱ የትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት አማካሪ የሆኑት አቶ በረከት አከለ የትምህርት ቤት ጤናና ምግብ ፕሮግራም በተመለከተ የባንኮክ ተሞክሮ ባቀረቡበት ወቅት እንደገለፁት የተቀናጀ የትምህርት ቤት ጤናና የምግብ ፕሮግራም የተማሪዎችን የትምህርት ውጤት ከመደገፍ በተጨማሪ  ትምህርት ቤት ጤናና ምግብ ጋር የተያያዘ የትምህርት ማህበረሰብ ግንዛቤ ማደግ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

 

በቀጣይነትም ለፕሮግራሙ ተግባራዊነት የቅንጅት ስራዎች በተለይም ሚነስቴር /ቤቱና የፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በየደረጃው ያሉ የመንግስት መዋቅሮች እንዲሁም ከልማት አጋ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በመድረኩ የተነሱ ክፍተቶች ለመሙላት ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

 

የዓለም አቀፍ ለህፃን  ዕድገት አጋር ድርጅት ፕሮግራም (PCD) ስራ አስካጅ ወሮ ለውራ አፕለባይ በአግባቡ የተቀረፀ የትምህርት ቤት ጤናና ምግብ ፕሮግራም ወጪ ቆጣቢና ውጤታማ መሆኑን በመናገር የሀገር በቀል የትምህርት ቤት ምገባ የተማሪዎች ውጤትን ከማሻሻል ባሻገር የግብርና ምርት ገበያ ለማሳደግ እንደሚረዳም ገልጸዋል፡፡

 

የትምህርት ቤት ጤናና ምግብ ፕሮግራም አተገባበሩ ላይ ያጋጠሙ መልካም ግኝቶች ችግሮችና የትኩረት አቅጣጫዎች የሚያሳዩ  ጥናቶች እንዲሁም የውጭ ሀገር ተሞክሮዎች ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

 

በመድረኩ ከሚኒስቴር /በቱ፣ ከፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና ከክልል ትምህርት ቢሮ  እንዲሁም ከዓለም አቀፍ የልማት ድርጅቶች የተውጣጡ ኃላፊዎች፣ ባለሙያዎችና የትምህርት ቤት ጤናና ምግብ ፕሮግራም ተጠሪዎች ተሳትፈዋል፡፡No comments yet. Be the first.
News

ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች ለሚሰጠው የመውጫ ምዘና / EXIT EXAM / በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ

በህክምናና በህግ ትምህርት ተሞክሮ ከፍተኛ ውጤት ያስገኘው የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ምዘና / EXIT EXAM / ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች እንደሚካሄድ የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታው ክቡር ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ አስታወቁ፡፡ የትምህርት ሚኒስትር ደኤታ ክቡር ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ከመጪው 2011 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገው የመውጫ ምዘና / EXIT EXAM / የከፍተኛ ትምህርት ምሩቃን በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው ተፈላጊውን ዕውቀት ክህሎትና አመለካከት እንዲላበሱ ያስችላል፡፡

የነጭ ሪቫን ቀን ተከበረ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር የተጠሪ ተቋማትና የዋናው ጊቢ ሠራተኞች በአንድ ላይ የነጭ ሪቨን ቀን አከበሩ፡፡ የነጭ ሪቫን ቀን ‹‹ በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶቸን ለመከላከልና ለማስወገድ የወንዶች አጋርነትን ማጠናከር ›› በሚል የዓመቱ መሪ ቃል በአለም አቀፍ ደረጃ ለ26ኛ በሀገራችን ደግሞ ለ12ኛ ጊዜ ከህዳር 16-27 ተከብሮ ይውላል ያሉት በትምህርት ሚኒስቴር የስርዓተ-ጾታ ዳይሬክቶሬት ባለሙያ የሆኑት አቶ ብርሃኑ ናቸው፡፡

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚካሄዱ የትምህርትና ሥልጠና ሥራዎች ውጤታማነት ተማሪዎች፣ መምህራን ፣ወላጆችና ህብረተሰቡ ኃላፊነታቸውን በላቀ ደረጃ ሊወጡ እንደሚገባ ተገለጸ

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚካሄዱ የትምህርትና ሥልጠና ሥራዎች ውጤታማነት ተማሪዎች፣ መምህራን ፣ወላጆችና ህብረተሰቡ ኃላፊነታቸውን በላቀ ደረጃ ሊወጡ እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ አስታወቁ፡፡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ህብረ-ብሔራዊነትና ኢትዮጵያዊነት የሚገነባባቸው ተቋማት እንጂ ተግባራቸው በጥቂት ችግር ፈጣሪዎች የሚስተጓጎል አለመሆኑንም ገለጹ 141ሺህ አዲስ ተማሪዎችን ጨምሮ ከ700 ሺህ በላይ ተማሪዎች በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመማር ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

ከ2011 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም የቅድመ ምረቃ ትምህርት መስኮች የብቃት መለኪያ አጠቃላይ ምዘና (የመውጫ ፈተና) ልተገበር ነው

ከ2011 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም የቅድመ ምርቃ ትምህርት መስኮች ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት የብቃት መለኪያ አጠቃላይ ምዘና (የመውጫ ፈተና) ወስደው አጥጋቢና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚጠበቅባቸው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የከፍተኛ ትምህርት ጥራትን በተለይም የምሩቃንን ብቃትና ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ አጠቃላይ ምዘና ወይም የመውጫ ፈተና መስጠት የምሩቃንን ዕውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት ለመመዘን የላቀ ሚና ከመጫወቱም በተጨማሪ የተመራቂ ተማሪዎች በራስ መተማመን ያጎለብታል፡፡

የምርምርና የፈጠራ ስራ ውድድር ኤግዚቪሽን ተካሄደ

የሂሳብና ሣይንስ ትምህርቶች ማሻሻያ ማዕከል ከስቴምስ ሲነርጂ ፣ከዩኔስኮ እና ከኢትዮጵያ ሣይንስ አካዳሚ ጋር በመተባበር "በሣይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ የበለፀገ ህብረተሰብ ለዘላቂ ሠላምና ልማት "በሚል መሪ ቃል አገር አቀፍ የምርምርና ፈጠራ ስራ ውድድር ኤግዚቪሽን በኢትዮጵያ ሣይንስ አካዳሚ ተካሄደ፡፡ የምርምርና የፈጠራ ስራ አውደ- ርዕይ መከፈቱን አስመልክቶ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት ፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ የኢትዮጵያ ሣይንስ አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር ሲሆኑ የኢትዮጵያ ሣይንስ አካዳሚ የኢትዮጵያን ሣይንስ ለማበልፀግ የተቋቋመ መሆኑን አስታውሰው ይህ ማዕከል የህብረተሰቡን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ እንዲሁም ቴክኖሎጂን የመጠቀም አቅሙን ለማጎልበት ለማስተማርና የሣይንስ ፖርሽን ለመፍጠር የተሰራ ሲሆን ቋሚ የሳይንስ ማዕከል ለመፍጠር ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው፡፡ በመሆኑም በቅርቡም የሳይንስ ማዕከሉ ወደ ስራ ይገባል በዚህም ወጣቱ ወደ ሣይንስ በሄደ ቁጥር የሀገራችን ተስፋ እየለመለመ ይሄዳል ብለዋል፡፡