News News

የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ አጭር ማብራሪያ

 
 1. በጥር ወር 2009 ዓ.ም. በሚኒስትሮች ምክር ቤት ለመንግስት ሰራተኞች የፀደቀው የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ ነው። በሐምሌ 2008 ለመምህራን የፀደቀው ማሻሻያ የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ ነው። ሁለቱም የደመወዝ ጭማሪ አይደለም።
 2. የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ የሚባለው ደመወዝን ከገበያ ጋር ለማቀራረብ የመንግስት የመክፈል አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚደረግ ማሻሻያ ነው። የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ ሲደረግ ቀድሞ ማስተካከያ የተደረገባቸውን ወይም የተሻለ ክፍያ የሚያገኙ ሠራተኞችን አይመለከትም። በሌላ በኩል የደመወዝ ጭማሪ ከመደበኛ የውጤት ተኮር ምዘና ውጤት ላይ ተመሥርቶ ለአንድ ሰራተኛ ከተመደበበት የሥራ ደረጃ የጣሪያ ደመወዝ ሳያልፍ  የሚደረግ መደበኛ የእርከን ደመወዝ ጭማሪ ነው። በዚህም ሠራተኛው ከነበረበት የመነሻ ወይም የእርከን ደመወዝ ወደ ቀጣዩ የእርከን ደመወዝ ላይ እንዲያርፍ የሚደረግበት አሰራር ነው። የኑሮ ውድነት ማካካሻ የሚባለው ደግሞ ወቅታዊ የገበያ ሁኔታ በሰራተኛው ኑሮ ላይ የሚያደርሰውን ጫና ለመቅረፍ የመንግስትን የመክፈል አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚደረግ የኑሮ ውድነት ማካካሻ ነው።  የደመወዝ ስኬል ማስተካከያም ሆነ የኑሮ ውድነት ማካካሻ ያለፉት 10 ዓመታት  ተሞክሮ የሚያሳየው በአማካይ በየሦስት ዓመቱ መደረጉን ነው።
 3. ቀደም ሲል የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ የተደረገላቸው ተቋማትና በልዩ ስኬል የዓላማ ፈፃሚዎች ደመወዝ ስኬል እየተስተናገዱ የነበሩ ተቋማት በዚህ ስኬል ማስተካከያ አልተካተቱም። እንደሚታወቀው ቀደም ሲል የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ የተደረገላቸው ተቋማት በዚሁ በጀት ዓመት መጀመሪያ ከስድስት ወራት በፊት የተከናወነ ነው። ስለሆነም የስኬል ማስተካከያ ከአገሪቱ ኢኮኖሚና የመክፈል አቅም ጋርም እንዲሁም ከአሰራርም አኳያ በየመንፈቁ ሊካሄድ የሚችል  አይደለም።
 4. በአሁኑ የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ ያልተካተቱ ተቋማት በሐምሌ 2008 የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ የተደረገላቸው [ዳኞች፣ዐቃበያን ህግ፣መምህራንና የአካዳሚ ሠራተኞች እና የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን] ሲሆኑ ሌሎች 33 ተቋማት በአንፃራዊ መልኩ በተለያዩ ጊዜያት ከሌላው የመንግሥት ሠራተኛ ከፍ ያለ የደመወዝ ስኬል ተፈቅዶላቸው የነበሩ ናቸው።

እነዚህም፡-

 1. የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዮት የተመራማሪዎች የደመወዝ ስኬል
 2. ብሔራዊ ኘላን ኮሚሽን የደመወዝ ስኬል
 3. የፖሊሲ ጥናት ምርምር ማዕከል የደመወዝ ስኬል
 4. የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን የደመወዝ ስኬል
 5. የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር የደመወዝ ስኬል
 6. ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የደመወዝ ስኬል
 7. የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የደመወዝ ስኬል
 8. የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የደመወዝ ስኬል
 9. የብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዮት የተመራማሪዎች የደመወዝ ስኬል
 10. ብሔራዊ  የአፈር ምርምር ላቦራቶሪ ተመራማሪዎች የደመወዝ ስኬል
 11. ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ምርምር ማዕከል የተመራማሪዎች የደመወዝ ስኬል
 12. የመንገድ ትራንስፖርት  ባለስልጣን የደመወዝ ስኬል
 13. የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር የደመወዝ ስኬል
 14. የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለስልጣን የደመወዝ ስኬል
 15. የደን ምርምር ኢንስቲትዮት የደመወዝ ስኬል
 16. የኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስቲትዮት የደመወዝ ስኬል
 17. የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የደመወዝ ስኬል
 18. የቡናና ሻይ ልማትና ግብይት ባለስልጣን የደመወዝ ስኬል
 19. የፌዴራል አነስተኛና መካከለኛ የማንፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዮት የደመወዝ ስኬል
 20. የከተሞች የሥራ እድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ የደመወዝ ስኬል
 21. የታላቁ የኢትጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ምክር ቤት የደመወዝ ስኬል
 22. ባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዮት የደመወዝ ስኬል
 23. ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የደመወዝ ስኬል
 24. ከፍተኛ ፍርድ ቤት የደመወዝ ስኬል
 25. የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የደመወዝ ስኬል
 26. የተቀናጀ መሠረተ ልማት ማስተባበሪያ ኤጀንሲ የደመወዝ ስኬል
 27. የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂያዊ ጥናት ኢንስቲትዮት የደመወዝ ስኬል
 28. የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የደመወዝ ስኬል
 29. የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኘሮጀክት ማኔጅመንት ኢንስቲትዮት የደመወዝ ስኬል
 30. የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ኤጀንሲ የደመወዝ ስኬል
 31. የኢትዮጵያ ኘሬስ ድርጅት የደመወዝ ስኬል
 32. የፋይናንስ ደህንንት መረጃ ማዕከል የደመወዝ ስኬል
 33. ብሔራዊ መረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የደመወዝ ስኬል

ስለሆነም ይህ የአሁኑ የመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ የሚመለከተው ሌሎች በፌዴራልና በክልል ያሉ በመንግሥት በጀት የሚተዳደሩ የመንግሥት ሠራተኞች፣ የፖሊስና መከላከያ ሠራዊት አባላት፣ የሕዝብ ተመራጮችንና ተሿሚዎችን ነው።  ይህም በተሟላ ጥናት ላይ የተመሠረተና የመንግሥትንም የመክፈል አቅም ያገናዘበ በመሆኑ ፍትሃዊ ነው።

 1. የፐብሊክ ሰርቫንቱ የአሁን የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ ዝቅተኛ ደመወዝ 582 ብር የነበረውን መነሻ ደመወዝ ወደ 860 ስኬሉን ከፍ የሚያደርግ እና መድረሻ ጣሪያ 1,439 ብር የሚያደርግ ነው።  ከፍተኛ ደመወዝ ፕሣ - 9 ሲሆን 5,781 ብር የነበረው መነሻው ወደ 7,647 በማሳደግ እና ጣሪያው 10,946 በማድረግ እስኬሉ ተሻሽሏል።
 2. የመምህራን ደመወዝ ስኬል ማስተካከያ በበጀት ዓመቱ / ሐምሌ 2008 ዓ.ም / መጀመሪያ መከናወኑ ይታወቃል።  ይህም መምህራን የሰው ኃይልን የመቅረፅ ትልቅ ተልዕኮ ያላቸው በመሆኑ የተለየ ትኩረት መስጠቱ አግባብ ነው።  ሌሎችንም ድጋፎች (የመኖሪያ ቤት፣ የትራንስፖርት ወ.ዘ.ተ) በሁሉም አካባቢዎች አቅም በፈቀደ መጠን ትኩረት ሰጥቶ ማሟላት ያስፈልጋል።  ከዚህ አኳያ የተጀመሩ ሥራዎች አበረታች ናቸው።  አሁን ለሌሎች ተቋማት የተከናወነ የደመወዝ ስኬል ማስተካከያም ቢሆን ከመምህራን የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ልዩነት ያለው ነው።
 3.  
 1. መሰናዶ ት/ቤት 2ኛ ድግሪ ያለው ጀማሪ መምህር 4,269 ብር ሲሆን 2ኛ ዲግሪ ያለው ጀማሪ ሠራተኛ በሌሎች ተቋማት 3,137 ብር ነው።  ይህ ሰባት ዕርከን ልዩነት ያለው ነው። 

እንዲሁም ከፍተኛ መሪ ርዕሰ መምህር 12,112 ብር የሚከፈለው ሲሆን በሌሎች መንግሥት ተቋማት ያለው መካከለኛ አመራር [ዳይሬክተር፣ ሥራ ሂደት ባለቤት፣ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወዘተ] 7,647 ብር ይከፈለዋል።ይህ ከአሥር እርከን በላይ ነው።

 1. በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በመጀመሪያ ዲግሪ በመምህርነት የተቀጠረ 4,662 ብር በሌሎች የመንግሥት ተቋማት 2,748 ብር ይከፈለዋል።  ይህ የ12 (አሥራ ሁለት) እርከን ልዩነት ያለው ነው።  በዚሁ መስክ ከፍተኛ መሪ መምህር III 11,720 ሲከፈለው በመንግሥት ተቋማት ያለ መካከለኛ አመራር [ዳይሬክተር፣ ሥራ ሂደት ባለቤት፣ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወዘተ] 7,647 ብር ይከፈለዋል።  ይህ ደግሞ ከአሥር እርከን በላይ ነው።
 2. በመጀመሪያ ዲግሪ ቴክኒካል ድሮዊንግ መምህር 4,085 ብር ሲከፈለው በሌሎች ተቋማት ያለው ግን 2,748 ብር ይከፈለዋል።  ይህ ደግሞ የዘጠኝ እርከን ልዩነት ያለው ነው።  በተመሳሳይ ዘርፍ ከፍተኛ መምህር 10,567 ብር ሲሆን በሌሎች ተቋማት 7,647 ብር ነው።  ይህ የዘጠኝ እርከን ልዩነት ነው።
 3. ከ9ኛ-10ኛ ክፍል ጀማሪ መምህር 3,137 ብር ሲሆን የመጀመሪያ ዲግሪ በሌሎች ተቋማት ጀማሪ 2,748 ብር ነው።  ይህም የሦስት እርከን ልዩነት ያለው ነው።  የከፍተኛ መሪ መምህር 8,539 ሲሆን በሌሎች ተቋማት መካከለኛ አመራር [ዳይሬክተር፣ ሥራ ሂደት ባለቤት፣ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወዘተ] ደመወዝ ግን 7,647 ነው።
 4. ከ1ኛ-8ኛ ክፍል ጀማሪ የዲፕሎማ መምህር 2,404 ብር ሲሆን በሌሎች ተቋማት 2,100 ብር ነው።  ይህም የሦስት እርከን ልዩነት ያለው ነው።
 5. የሰርተፍኬት መምህራን ጀማሪ መምህር 1,828 ብር ሲሆን በሌሎች ተቋማት 1,370 ብር ነው።  ይህ የስድስት እርከን ልዩነት ያለው ነው።

ስለሆነም በአጠቃላይ ሲታይ መንግሥት ለመምህራን የሰጠው ትኩረት የተለየ እና ተገቢ ነው።  በቀጣይነትም በተለይ የመኖሪያ ቤትና መሰል ድጋፎች በተሟላ መልኩ ደረጃ በደረጃ እየተሟሉ መሄድ ይኖርባቸዋል።

ከላይ ለማብራራት እንደተሞከረው አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የፐብሊክ ሰርቫንቱን የደመወዝ ስኬል ማስተካከያን እንደ ደመወዝ ጭማሪ በመውሰድ መምህራን ይመለከተናል በሚል በአንዳንዶች ዘንድ የሚራመደው የተሳሳተ ሀሳብን ማስተካከል ያስፈልጋል።

በዚህ አጋጣሚ መላው መምህራን እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋን ለማፍራት የምታደርጉትን ትጋት በማጠናከር በሀገራችን የሕዳሴ ጉዞ ላይ አሻራችሁን  ለማሳረፍ  እንድትረባረቡ ጥሪ እናቀርባለን። 

የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት እና ትምህርት ሚኒስቴር በጋራ የተሰጠ ማብራሪያ


No comments yet. Be the first.
News

የ2009 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ (የ10ኛ ክፍል) ብሔራዊ ፈተና ከግንቦት 23- 25 እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና (የ12ኛ ክፍል) ከግንቦት 28 እስከ ሰኔ 1 2009 ዓ.ም. ይሰጣሉ

የትምህርት ሚኒስቴር የ2009 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ (የ10ኛ ክፍል) ብሔራዊ ፈተና ከግንቦት 23- 25 እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተናዎች (የ12ኛ ክፍል) ከግንቦት 28 እስከ ሰኔ 1 2009 ዓ.ም. እንደሚሰጡ ገለጸ፡፡ የፈተናው አጠቃላይ ዝግጅት የተጠናቀቀ ሲሆን በሀገሪቱ ለሚገኙ ተፈታኞች 3,467 የፈተና ጣቢያዎች ተዘጋጅተዋል፡፡ በዚህ ዓመትም ከ1.2 ሚሊየን በላይ የ10ኛ ክፍል እንዲሁም ከ288ሺህ በላይ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ይኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር በተፈጥሮ ሳይንስና ምህድስና ትምህርት መስክ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ሴት ተማሪዎችን ሸለመ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሥርዓተ ጾታ ዳይሬክቶሬት ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የሥርዓተ ጾታና ባለ ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር በተፈጥሮ ሳይንስና ምህድስና ትምህርት መስክ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከአንደኛ እስከ አምስተኛ አመት ያሉ ሴት ተማሪዎች፣ ድጋፍ ላደረጉላቸው መምህራንን እና አመራሮች የማበረታቻ ሽልማት ሰጠ፡፡ በዩኒቨርሲቲው የመሰብሰቢያ አደራሽ ...

በሙያ ፍቃድ የምዘና ውጤት ትንተናና በመምህራን ትምህርት ኮሌጆች እውቅና አሰጣጥ ስታንዳርዶች ዙሪያ ምክክር መድረክ ተካሄደ

ሀገራችን የሙያ ፍቃድ አሰጣጥና እድሳት ስርዓት በመዘርጋት የመምራን፣ የርዕሰ መምህራንና የሱፐርቫይሮች ሙያዊ ብቃት ምዘና ሂደትን በወጥነት ለመተግበርና በሙያ ፍቃድ አሰጣጥ የአደረጃጀቶችን ሚናና የፈጻሚ ባለድርሻ አካለላትን ተግባርና ኃላፊነት ለይቶ ለማሳወቅና ተጠያቂነትን ለማስፈን የሚየስችል የአሰራር ስርዓት ዘርግታ እየሰራች ትገኛለች፡፡ በሙያ ፍቃድ አሰጣጥ ስርዓት ውስጥ ሶስት የሙያ ፍቃድ አይነቶች አሉ፡፡ እነዚህም፦ አንደኛው የመጀመሪያ ሙያ ፍቃድ ለጀማሪ መምህራንና በትምህርት ተቋማት አመራርነት ሰልጥነው ወደሙያው ለሚገቡ እንዲሁም ለደረጃው የብቃት መመዘኛ ላሟሉ የሚሰጥ ፣ ሁለተኛው ሙሉ የሙያ ፍቃድ፥ ለአምስት አመት የሚያገለግል ሆኖ የመጀመሪያ ሙያ ፍቃድ በማግኘት ሲሠሩ ቆይተው ላጠናቀቁ የሚሰጥ ሲሆን የሦሥተኛው ደግሞ ቋሚ የሙያ ፍቃድ ነው፡፡ ይህ ፍቃድ ሙሉ የሙያ ፍቃድ ከያዙ በኋላ ለደረጃው የሚመጥን አገልግሎት አጠናቀው የሙያ ፍቃድ ብቃት መመዘኛ ላሟሉ መምህራን፣ ለርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የሚሰጥና በየአምስት አመት የሚታደስ ቋሚ የሙያ ፍቃድ ነው፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር የትራፊክ አደጋን ትርጉም ባለው መልኩ ለመቀነስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከመንገድ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር “ከትራፊክ አደጋ የጸዳ የትራንስፖርት አገልግሎት ለሀገራዊ ህዳሴ“ በሚል ሀገራዊ መሪ ቃል በሀገር ደረጃ የትራፊክ አደጋን ትርጉም ባለው መልኩ ለመቀነስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ ያካሄደው በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አደራሽ ሚያዝያ 20/2009 ዓ∙ም ነበር። የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚስትር ዴኤታ የሆኑት የተከበሩ ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ መድረኩን በእንኳን ዳህና መጣችሁ ንግግር በከፈቱበት ወቅት እንደተናገሩት የትራፊክ አደጋን ከምንጩ በመቀነስ የህዝባችንን ህይወት፣አካልና ንብረት፤እንዲሁም የሀገሪቱን ሀብት ከጥፋት ለመታደግ መላው ህብረተሰብ በትራፊክ ደህንነት ዙሪያ በባለቤትነት ስሜት እንድንቀሳቀስ ማድረግና ከዚህ አንጻር ዜጎችን በመልካም ሥነ-ምግባር መቅረፅ በአሁኑ ወቅት እጅግ በጣም አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል። በአሁን ወቅት በትምህርት ዘርፉ ውስጥ በተለያዩ የትምህርት እርከኖች ላይ 30 ሚሊዮን የሚጠጉ ተማሪዎች፣ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ መምህራን፣ከተማሪዎች በስተጀርባ ያሉ በርካታ ወላጆችና መደበኛ ባልሆነ የተቀናጀ የጎልማሶች ትምህርት ላይ እየተሳተፉ ያሉ በርካታ ሠልጣኞች እንዳሉ ጠቅሰው ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በሚገባ በመቀናጀት ከዚህ በፊት ሲሠራ ከነበረው ይበልጥ ሥራውን በማስፋትና በማጠናከር ከተሠራ በሀገር ደረጃ መሠረታዊ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል አስገንዝበዋል።

የተፋጠነ የትምህርት ቤት ዝግጁነት የትምህርት አቀራረብ ሥነ-ዘዴ እንደ አንድ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ማስፋፊያ አመራጭ ተወስዶ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንድተገበር የምመክር አውደ ጥናት ተካሄደ

የትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል ከ2007 ዓ.ም ክረምት ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተተገበረ ያለውን የተፋጠነ የትምህርት ቤት ዝግጁነት የቅድመ መደበኛ ትምህርት አቀራረብ ውጤታማነትን ለማስተዋወቅና በሀገር አቀፍ ደረጃ ለማስፋት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውጪ ከሁሉም ክልሎች፤ ከድሬደዋ ከተማ አስተዳደር፣ ከዩኒሴፍ ኢትዮጵያ እና ከህጻናት አድን ድርጅት እንዲሁም ከትምህርት ሚኒስቴር የተውጣጡ የሥራ ኃላፊዎችና የትምህርት ባለሙያዎች የተሳተፉበት አውደ ጥናት ሚያዚያ 2 እና 3/2009 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አደራሽ ተካሄደ። ይህ ፕሮግራም ከአራቱ የቅድመ መደበኛ ትምህርት አሰጣጥ ሥነ-ዘዴ መካከል አንዱ ሲሆን በሦስቱም (መዋዕለ ህጻናት፤ ኦ ክፍልና ህጻን ለህጻን) የቅድመ መደበኛ ትምህርት አሰጣጥ ዘዴ ተጠቅመው ለመደበኛ ትምህርት ቅድመ ዝግጅት ያላደረጉትን እድሜያቸው ስድስት ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ህጻናትን በስምንት ሳምንታት ውስጥ ለመደበኛ ትምህርት ዝግጁ ማድረግ ያሚያስችል ፕሮግራም ነው።

Communication and Media Communication and Media

Communication Address:

Tel: +251-11-156-14-94

Fax: