የትምህርት ዘርፍ ወቅታዊ ዜናዎች እና መረጃዎች

የ2009 የትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት ይፋ ሆነ

በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ በመደበኛና በማታው የትምህርት መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ለተከታተሉ ተማሪዎች ለወንዶች 354 እና በላይ፤ ለሴቶች 340 እና በላይ፣ ሁሉም የግል ተፈታኝ ወንዶች 360 እና በላይ፤ ለሴቶች 355 እና በላይ፣ በአወንታዊ ድጋፍ መሰረት ለታዳጊና የአርብቶ አደር ተማሪዎች ለወንዶች 340 እና በላይ፤ ለሴቶች 335 እና በላይ፣ ሁሉም መስማት ለተሳናቸው ተማሪዎች ወንዶችም ሴቶችም 297 እና በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ይመደባሉ፡፡ በማህራዊ ሳይንስ ትምህርት ዘርፍ ሁሉም መደበኛና የማታው የትምህርት መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ለተከታተሉ ተማሪዎች...

የትምህርት ዘርፍ ልማት የአምስት አመት እቅድ በተናበበና በተቀናጀ መልኩ ይተገበራል

የሀገራችንን ህዳሴ ለማረጋገጥ የሚደረገውን ዘርፈ ብዙ ጥረት ዳር ለማድረስ የአምስት ዓመቱን የትምህርት ዘርፍ ልማት እቅድ በተናበበና በተቀናጀ መልኩ መተግበር ተገቢ እንደሆነ በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ አስታወቁ፡፡ በአዳማ ከተማ አባገዳ አዳራሽ ለአራት ቀናት ሲካሄድ በቆየው የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሀገራዊ የህዝብ የንቅናቄ መድረክ መገባደጃ ላይ ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ የአምስት ዓመቱን የትምህርት ዘርፍ ልማት እቅድ ለንቅናቄ መድረኩ ተሳታፊዎች ባቀረቡበት ወቅት ሀገሪቱ የምትፈልገውን ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋ በብቃትና በጥራት በማፍራት የሀገራችንን ህዳሴ...

በአገራችን በአሁኑ ወቅት 28 ሚሊዬን ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው

ባለፉት 25 ዓመታት ለሃገራችን ዜጎች ትምህርትን በፍትሐዊነት ለማዳረስ በተደረገው ጥረት በአሁኑ ወቅት 28 ሚሊዬን ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ላይ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ አስታወቁ፡፡ ሚኒስትሩ የትምህርትን ተገቢነት፣ ፍትሐዊነትና ጥራትን ለማምጣት በአዳማ ከተማ በተዘጋጀው የህዝብ ንቅናቄ መድረክ ዜጎች ከቅድመ መደበኛ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ድረስ ፍትሐዊ ትምህርት እንዲያገኙ ከአካባቢው ነባራዊ ሁኔታ ጋር በሚመጥን መልኩ ቢያንስ በየ 2.5 ኪሎ ሜትር ርቀት አንድ ትምህርት ቤት በመሰራቱ በሴቶችና በወንዶች፣ በገጠርና በከተማ፣ ልዩ ፍላጎት ባላቸው ዜጎች የትምህርት...

ለትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ውጤታማነት ጠንካራ የልማት ሰራዊት ግንባታ አስፈላጊ ነው

የትምህርትና ስልጠና ዘርፉን ስኬታማና የሚፈለገውን ውጤት እንዲያመጣ ለማስቻል ጠንካራ ቁመና ያለው የትምህርት ልማት ሰራዊት ግንባታ ላይ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ አንዳንድ ክልሎች አስታወቁ፡፡ ክልሎች የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሀገራዊ የህዝብ ንቅናቄ መድረኩን አስመልክቶ በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የ2009 ዓ.ም የህዝብ ንቅናቄ ማቀጣጠያ ሰነድ እና በመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት አፈፃፀም መመሪያ፣ በስነ ዜጋና ስነ ምግባር አተገባበር ሰነድ እንዲሁም በሌሎች ሰነዶች ላይ ውይይት ባካሄዱበት ወቅት ክልሎች ያሉበትን የአፈፃፀም ደረጃ ለማወቅና በ2009 ዓ.ም ምን ላይ...

የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሀገራዊ የህዝብ ንቅናቄ መድረክ በአዳማ ከተማ አባገዳ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጀመረ

ለአራት ተከታታይ ቀናት በሚካሄደው ሀገራዊ የህዝብ ንቅናቄ መድረክ ከሁሉም ክልልና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች፣ ከተለያዩ የህዝብ ክንፍ አካላት እንዲሁም ሌሎች አጋርና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡ የንቅናቄ መድረኩን መጀመር አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስቴር አጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ የሃገራችንን ልማትና ዴሞክራሲ የሚያስቀጥል ትውልድ ለመፍጠር በትምህርትና ስልጠና ዘርፉ ትኩረት ተሰጥቶ ሲሰራ መቆየቱንና አበረታች ለውጥ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡ የትምህርት ሽፋንን ለማሳደግና የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ባለፉት ዓመታት በተደረገው ጥረት በገጠርና...
Showing 1 - 5 of 33 results.
Items per Page 5
of 7